በጤና ሴክተር የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሰረታዊነት መፍታት አስፈላጊ ነው ÷ አቶ አጥናፉ ኃይሌ::

Spread the love

የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ሰራተኞችና ባለሙያዎች የማጥራት ግምገማ እና ሂስ ግለ ሂስ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል::

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት አሁን ላይ በሁሉም የመንግስት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶ ታቅዶ እየተሰራ ያለበት ወቅት ነው ብለዋል